እንኳን ለ121ኛዉ የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሳችሁ
የሙሉዓለም ባህል ማዕከል ይህን ታሪካዊ የድል በዓል ጠብቀን ለመጭዉ ትዉልድ ለማስተላለፍ ኪነ-ጥበብ ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን በመገንዘብ ዛሬም እንደትናንቱ ባህል ማዕከሉ ተግቶ ይሰራል፡፡
የሙሉዓለም ባህል ማእከል በ2012 በክልሉ ተመራጭ የባህል አምባ ለመሆን ያስቀመጠዉን ራዕይ ለማሳካት ሰራተኛዉና አመራሩ ተቀናጅቶ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
ባህል ማዕከሉ ባስገነባዉ አዲስ ስቱዲዮ የተለያዩ የቀረፃ ስራዎችን እየሰራ ይገኛል፡፡ ከነዚህ መካከል
 የሬድዮ ስፖት
 አጫጭር ድራማዎችና ሌሎችም የኪነ-ጥበብ ስራዎች ከሌሎች አጋር አካላት ጋር ተቀናጅተን በመስራት ለጋራ ሀገራዊ ልማት እየተረባረብን እንገኛለን፡፡ በተጨማሪም ባህል ማዕከሉ ከ1.5 ሚሊዮን ብር በላይ የዘመናዊ ሙዚቃ መሳሪያወች ግዥ በመፈፀም ዘመናዊ የሙዚቃ ቡድኑን እያጠናከረ ይገኛል ፡፡
 የክልሉ የባህል አምባሳደር የሆነዉየባህል ቡድናችን በሃገራችንና ከሃገራችን ዉጭ ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በጋራበመስራት የክልሉን ብሎም የሃገራችን ባህል በማስተዋወቅ ላይ ይገኛል፡፡ በቀጣይም መንግስት የጀመረዉን ሰላም ዲሞክራሲና ልማት አጠናክሮ ለማስቀጠል ከባህል ማዕከሉ የሚጠበቀዉን ኪነ-ጥበባዊ ስራዎች ለማበርከት በዚህ ታሪካዊ የድል በዓል ቃላችን እናድሳለን፡፡
የአድዋን ድል ጠብቀን የኪነ-ጥበብ ህዳሴን እናረጋግጣለን
መልካም የአድዋ ድል በዓል
የሙሉዓለም ባህል ማዕከል፡፡