በስልጠና አቅምን በማሳደግ ለኪነ-ጥበብ ህዳሴ እንተጋለን!
የሙሉዓለም ባህል ማዕከል ከባህልና ቱሪዝም ቢሮ ጋር በጋራ በመተባበር በሙሉዓለም ባህል ማዕከል ከጥር 15/2009 ዓ/ም ጀምሮ እስከ የካቲት 05/2009 ዓ/ም ከሁሉም ዞኖች ለመጡ የባህልና ቱሪዝም መምሪያ የቴአትርና ትወና ባለሙያዎች፣ ከጎንደር፣ ከባ/ዳርና ከደሴ እንዲሁም ከሙሉዓለም ባህል ማዕከል፣ ከባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና በባህር ዳር ከተማ ከሚገኙ አማተር ክበቦች መካከል የተወሰኑትን በመምረጥ የስልጠናውን ዕድል እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል፡፡
ስልጠናው በተግባራዊ ትምህርት የተደገፈ በመሆኑ ለባለሙያዎች የሚኖረው ፋይዳ እጅግ የጎላ መሆኑ አያጠያይቅም፡፡ የሙሉዓለም ባህል ማዕከል ከተቋቋመበት አላማ አንፃር የክልሉን ባህላዊ፣ ትውፊታዊ የኪነ-ጥበብ ዕሴቶችን በማጎልበት ህ/ሰቡን እያዝናኑ ማስተማር እንደመሆኑ ይህ ስልጠና የባለሙያዎችን አቅም በማሳደግ ረገድ የሚኖረው ፋይዳ በእጅጉ የጎላ ነው፡፡ ስልጠናው ለሙሉዓለም ባህል ማዕከል፣ ለባህልና ቱሪዝም ቢሮና ለአማተሮች የተሰጠ እንደመሆኑ የዞን ባለሙያዎች ስልጠናውን ከጨረሱ በኋላ ለወረዳ ባለሙያዎች እንደሚሰጡ ይጠበቃል፡፡ በአጠቃላይ ኪነ-ጥበብ ለተጀመረው ሃገራዊ የባህል የህዳሴ ጉዞ የሚኖረው ጉልህ ሚና ከፍተኛ በመሆኑ እያዝናኑ ለማስተማር ይህ አይነት ስልጠና ወደፊትም ተጠናክሮ በመቀጠል የባለሙያውን አቅም በማሳደግ የኪነ-ጥበብ ህዳሴን ዕውን ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡
የስልጠና ተሳታፊዎች
ከሙሉዓለም ባህል ማዕከል ከዞን የቴአትር ኤክስፐርቶች ከባ/ዳር ከተማ ማህበራትና አማተሮች
ጠቅላላ ተሳታፊዎች
ወ = 10 ወ = 8 ወ = 3
ወ = 21
ሴ = 5 ሴ = 1
ሴ = 2 ሴ = 8
ድ = 15 ድ = 9 ድ = 5
ድ = 29
በሙሉዓለም የባህል ማዕከል
የባህልና ኪነ-ጥበብ ስራዎች
የፕሮሞሽንና ፕሮግራም ዋና የስራ ሂደት የተዘጋጀ
የካቲት 2009 ዓ/ም
ባህር ዳር