ከወዲሁ ፕሮግራመዎን ያስተካክሉ!! ዕሁድ ጥቅምት 27/2015 ዓ.ም ከቀኑ በ8:00 ጀምሮ ጉማ ትውፊታዊ ቴአትር በሙሉዓለም የአማራ ባህል ማዕከል ለይታ ይበቃል ። ቤተሰቤዎን እና ጓደኛዎን ይጋብዙ ። አትርፈው ይመለሳሉ ።
ወላጆች ልጆችዎን ዕሁድን የት ለማዝናናት አስበዋል?? ሁሌም የልጆቸዎ ደስታ ደስታችን ነው ። ሙሉዓለም የአማራ ባህል ማዕከል ልጆችን በመልካም ስነ-ምግባር ታንፀው እንዲያድጉ የሚያስተምርና ቁምነገር የሚያስጨብጥ አዲስ የህፃናት ቴአትር አዘጋጅቷል ። ከእርሰዎ የሚጠበቀው ፕሮግራመዎን ከወዲሁ ማስተካከል ብቻ!! የጫካዋ እመቤት እያዝናና ቁም ነገር የሚያስጨብጥ የህፃናት ቴአትር በሙሉዓለም የአማራ ባህል ማዕከል እሁድ ጥቅምት 27/2015 ዓ.ም ከጥዋቱ 4:00 ጀምሮ ከተለያዩ […]
በ10ኛው የጣና ፎረም ጉባኤ ለመሳተፍ ለመጡ እንግዶች በባሕር ዳር አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያና በአቫንቲ ሆቴል ደማቅ አቀባበል ተደረገ በክልላትን መዲና በሆኘችው ውቢቱ ባሕር ዳር ከተማ ከጥቅምት 4-6/2015 በሚካሄደው የጣና ፎረም ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ለመጡ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና አመራሮች እንዲሁም ጥሪ ለተደረገላቸው የክብር እንግዶች በባሕር ዳር አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ […]
የሙሉዓለም የአማራ ባህል ማዕከል በየወሩ የሚያዘጋጀውን የአማራ ለዛ የኪነ-ጥበብ ምሽት ጥቅምት 18/2015 ዓ.ም በሙሉዓለም የአማራ ባህል ማዕከል በድምቀት አካሂዷል። ከወር በፊት በሞት ያጣነውን አርትስት ማዲንጎ አፈወርቅን የሚዘክሩ የተመረጡ የራሱን የሙዚቃ ስራዎችበማዕከሉ የዘመናዊ የሙዚቃ ቡድን ፣በተወዳጅ ገጣሚያን ተለያዩ የግጥም ስራዎች በማዕከሉ የባህል መሳሪያ ተጫዋቾች አጃቢነት እና በአርቲስት መላኩ ታደሰ የተዘጋጀ አቢሲኒያ የባህል የውዝዋዌ ቡድን እና ሌሎች […]
ወላጆች ልጆቸዎን ዕሁድ የት ለማዝናናት አስበዋል?? ሁሌም የልጆቸዎ ደስታ ደስታችን ነው ። ሙሉዓለም የአማራ ባህል ማዕከል ልጆችን በመልካም ስነ-ምግባር ታንፀው እንዳያድጉ የሚያስተምር አዲስ የህፃናት ቴአትር አዘጋጅቷል ። ከእርሰዎ የሚጠበቀው ፕሮግራመዎን ከወዲሁ ማስተካከል ብቻ!! የጫካዋ እመቤት እያዝናና ቁም ነገር የሚያስጨብጥ የህፃናት ቴአትር በሙሉዓለም የአማራ ባህል ማዕከል እሁድ ጥቅምት 13/2015 ዓ.ም ከጥዋቱ 4:00 ጀምሮ ከተለያዮ ጨዋታዎች ጋር […]
በእውነት እንዳያመልጠዎ!!! ለቴአትር አፍቃሪያን ጥበብ ለናፈቀ ተዉኔት ለተጠማ “ጉማ!!” ትዉፊታዊ ቴአትር በደራሲያን ደሳለኝ ድረስ እና ንብረት ያለዉ ተደርሶ በዋና አዘጋጅ አባይነህ በለጠ እና በረዳት አዘጋጅ አመልማል ተክሉ በግሩም ሁኔታ የተዘጋጀዉ “ጉማ!!” ትዉፊታዊ ቴአትር በፕሮዳክሽን ማናጀርነት ይስማዉ የኋላ የተጠበበት የመድረክ ፈርጥና ጌጥ የሆኑ በርካታ አንጋፋና ወጣት ከያኒያን ድንቅ የትወና ብቃት ያሳዩበት “ጉማ!!”ትዉፊታዊ ቴአትር በቅርብ ቀን ለዕይታ […]
ልዩ የምረቃ ዝግጅት በሙሉዓለም የአማራ ባህልና የኪነ ጥበብ ማዕከል ማዕከሉ ከሐምሌ 18 እስከ ነሀሴ 25/2014 ዓ.ም ለ38 ቀናት ያሰለጠናቸውን ተተኪ የኪነ-ጥበብ ከያኒያንን ሀሙስ በ26/12/2014 ዓ.ም. በልዩ ልዩ የኪነ-ጥበብ ዝግጅቶች ያስመርቃል፡፡ በመሆኑም ከ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በማዕከሉ ተገኝተው እንዲታደሙ ተጋብዘዋል፡፡
ሙሉዓለም የአማራ ባህልና ኪነ-ጥበባት ማዕከል ተተኪ የኪነ-ጥበብ ሙያተኞችን ለማፍራት ስልጠና እየሰጠ ነዉ፡፡ በማዕከሉ ትውን ጥበባት ጥናትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በሙዚቃም ሆነ በቴአትር ዘርፍ ተተኪ የኪነ-ጥበብ ከያኒያንን ለማፍራት የሚያስችል፣ ክፍተት የለየና አቅምን ሊያጎለብት የሚችል ተግባራዊ ስልጠና ከሐምሌ 18/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ የዳይሬክቶሬቱ የትያትርና የሙዚቃ ስልጠና ቡድን አስተባባሪ ወ/ት ትግስት ማሩ […]