በእውነት እንዳያመልጠዎ!!! ለቴአትር አፍቃሪያን ጥበብ ለናፈቀ ተዉኔት ለተጠማ “ጉማ!!” ትዉፊታዊ ቴአትር በደራሲያን ደሳለኝ ድረስ እና ንብረት ያለዉ ተደርሶ በዋና አዘጋጅ አባይነህ በለጠ እና በረዳት አዘጋጅ አመልማል ተክሉ በግሩም ሁኔታ የተዘጋጀዉ “ጉማ!!” ትዉፊታዊ ቴአትር በፕሮዳክሽን ማናጀርነት ይስማዉ የኋላ የተጠበበት የመድረክ ፈርጥና ጌጥ የሆኑ በርካታ አንጋፋና ወጣት ከያኒያን ድንቅ የትወና ብቃት ያሳዩበት “ጉማ!!”ትዉፊታዊ ቴአትር በቅርብ ቀን ለዕይታ […]
ልዩ የምረቃ ዝግጅት በሙሉዓለም የአማራ ባህልና የኪነ ጥበብ ማዕከል ማዕከሉ ከሐምሌ 18 እስከ ነሀሴ 25/2014 ዓ.ም ለ38 ቀናት ያሰለጠናቸውን ተተኪ የኪነ-ጥበብ ከያኒያንን ሀሙስ በ26/12/2014 ዓ.ም. በልዩ ልዩ የኪነ-ጥበብ ዝግጅቶች ያስመርቃል፡፡ በመሆኑም ከ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በማዕከሉ ተገኝተው እንዲታደሙ ተጋብዘዋል፡፡
ሙሉዓለም የአማራ ባህልና ኪነ-ጥበባት ማዕከል ተተኪ የኪነ-ጥበብ ሙያተኞችን ለማፍራት ስልጠና እየሰጠ ነዉ፡፡ በማዕከሉ ትውን ጥበባት ጥናትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በሙዚቃም ሆነ በቴአትር ዘርፍ ተተኪ የኪነ-ጥበብ ከያኒያንን ለማፍራት የሚያስችል፣ ክፍተት የለየና አቅምን ሊያጎለብት የሚችል ተግባራዊ ስልጠና ከሐምሌ 18/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ የዳይሬክቶሬቱ የትያትርና የሙዚቃ ስልጠና ቡድን አስተባባሪ ወ/ት ትግስት ማሩ […]
ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ተተኪ የኪነ-ጥበብ ሙያተኞችን ለማፍራት ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ በማዕከሉ ትውፊታዊ ትውን ጥበባት ጥናት፣ምርምርና ስልጠና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በሙዚቃም ሆነ በቴአትር ዘርፍ ተተኪ የኪነ-ጥበብ ከያኒያንን ለማፍራት የሚያስችል፣ ክፍተት የለየና አቅምን ሊያጎለብት የሚችል ተግባራዊ ስልጠና ከመስከረም 18/2014 ዓ.ም ጀምሮ እየሰጠ ይገኛል፡፡የስልጠናው የቆይታ ጊዜ ለ25 ቀናት የሚቆይ ሲሆን እስከ ጥቅምት 12/2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ታውቋል፡፡ ማዕከሉ […]