ማዕከሉ በአሁኑ ወቅት በአንድ ዋና ዳይሬክተር፣በ6 ዳይሬክቶሬቶች፤በ3 የስራ ክፍሎች ተደራጅቶ ተግባራትን እያከናወነ የሚገኝ ሲሆን ከላይ በተቀመጡት ዳይሬክቶሬቶችና የስራ ክፍሎች እንዲሁም ዋና ዳይሬክተሩን ጨምሮ165 የስራ መደቦች የሚገኙ ሲሆን 106 የስራ መደቦችን በማሟላት አገልግሎት በመስጠትና ተደራሽ ለመሆን ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡
ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ከላይ በተጠቀሱት የስራ ክፍሎች ከ110 በላይ ሠራተኞች ያሉት ሲሆን የሚያከናዉናቸዉንም የኪነ-ጥበብ ተግባራት ተደራሽ ለማድረግ በሰለጠነና በተቀናጀ ሁኔታ በተቋሙ ዋና ዳይሬክተር መሪነት የክልሉም ሆነ የሀገራችን ህብረተሰብ በኪነ-ጥበባት የፈጠራ ዉጤቶች እየተዝናና የሚማሩባቸዉን፣ እዉቀት የሚያገኙባቸዉን እና ሀሳባቸዉን የሚገልፁባቸዉ መድረኮች በመፍጠርና በማመቻቸት ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ልዩነታቸዉ፣ ዉበታቸዉ፣ ዉበታቸዉ አንድነታቸዉን ሳይገድበዉ እና የተዋህደዉ አንድነታቸዉ ደግሞ ፍፁም ኢትዮጵያዊ ሆኖ እንዲቀጥል ሲሰራ ቆይቷል፡፡ ኢትዮጵያዉያን በባህላቸዉ እንዲኮሩ የባህል እሴቶቻቸዉ ተጠብቀዉ በሀገር አቀፍ ደረጃ ብቻ ሳይሆን በመላዉ ዓለም ለማስተዋወቅና የኪነ-ጥበብ ዘርፍ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር ለማድረግ ፍትሀዊና ተጠያቂነት የሰፈነበት አሰራር ዘርግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡
በባህል ማዕከሉ ያሉ የስራ ክፍሎች
ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ያቀደዉን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት አንጋፋና ወጣት የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች በመያዝ እንዲሁም በሚከተሉት የስራ ክፍሎች ተዋቅሮ በርካታ የኪነ-ጥበብ ስራዎች ሲያከናዉን ቆይቷል፡፡ አሁንም በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
የስራ ክፍሎቹም፡-