ሙሉዓለም የአማራ ባህልና ኪነ-ጥበባት ማዕከል ተተኪ የኪነ-ጥበብ ሙያተኞችን ለማፍራት ስልጠና እየሰጠ ነዉ፡፡ በማዕከሉ ትውን ጥበባት ጥናትና ስልጠና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በሙዚቃም ሆነ በቴአትር ዘርፍ ተተኪ የኪነ-ጥበብ ከያኒያንን ለማፍራት የሚያስችል፣ ክፍተት የለየና አቅምን ሊያጎለብት የሚችል ተግባራዊ ስልጠና ከሐምሌ 18/2014 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወር የሚቆይ ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡ የዳይሬክቶሬቱ የትያትርና የሙዚቃ ስልጠና ቡድን አስተባባሪ ወ/ት ትግስት ማሩ […]