በ10ኛው የጣና ፎረም ጉባኤ ለመሳተፍ ለመጡ እንግዶች በባሕር ዳር አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያና በአቫንቲ ሆቴል ደማቅ አቀባበል ተደረገ
በክልላትን መዲና በሆኘችው ውቢቱ ባሕር ዳር ከተማ ከጥቅምት 4-6/2015 በሚካሄደው የጣና ፎረም ጉባኤ ላይ ለመሳተፍ ለመጡ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎችና አመራሮች እንዲሁም ጥሪ ለተደረገላቸው የክብር እንግዶች በባሕር ዳር አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአማራ ብሔራዊ ክልለዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳደር የተከበሩ ዶ/ር ይልቃል ከፋለ እና ሌሎች የክልላችን ከፍተኛ የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል። በእንግዳ አቀባበል ስነ-ስርዓት ላይ የሙሉዓለም የአማራ የባህል ማዕከል፣ የግሽ አባይ የባህል ቡድን እና የአቢሲኒያ የባህል ውዝዋዜ ቡድን ወጣትና አንጋፋ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች ፈጠራ የታከለበት የተለያዩ የባህል ሙዚቃና ውዝዋዜ በማቅረብ ለእንግዶች ደማቅ አቀባበል አድርገዋል ።
ባሕር ዳር
03/02/2015 ዓ.ም