የሙሉዓለም የአማራ ባህል ማዕከል በየወሩ የሚያዘጋጀውን የአማራ ለዛ የኪነ-ጥበብ ምሽት ጥቅምት 18/2015 ዓ.ም በሙሉዓለም የአማራ ባህል ማዕከል በድምቀት አካሂዷል። ከወር በፊት በሞት ያጣነውን አርትስት ማዲንጎ አፈወርቅን የሚዘክሩ የተመረጡ የራሱን የሙዚቃ ስራዎችበማዕከሉ የዘመናዊ የሙዚቃ ቡድን ፣በተወዳጅ ገጣሚያን ተለያዩ የግጥም ስራዎች በማዕከሉ የባህል መሳሪያ ተጫዋቾች አጃቢነት እና በአርቲስት መላኩ ታደሰ የተዘጋጀ አቢሲኒያ የባህል የውዝዋዌ ቡድን እና ሌሎች አርቲስቶች የተሳተፋበት ከያኒዉ የተሰኘ ሙዚቃዊ ቴአትር ለታዳሚያን አቀርቧል። የሙሉዓለም የአማራ ባህል ማዕከል ተወካይ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙላት ዋለ እንደገለፁት አርቲስቱን በተለያዩ 3 ዝግጅቶች ማለትም በሻማ ማብራት፣ ቤተሰቦችን እና የሙያ ባልደረቦችን በማስተዛዘን እና በኪነ-ጥበብ ዝግጅቶች መዘከር የታሰቀው በዚህ አጭር እድሜው ከእድሜው በላይ ዘመን ተሻጋሪ የሆኑ የሙዚቃ ስራዎችን በመስራቱ መሆኑን ገልፀው እኛም በተሰማራንበት ዘርፍ ውጤታማ ስራ በመስራት አሻራችን ለተተኪው ትውልድ ማስተላለፍ ይኖርብናል ሲሉ በዕለቱ ለታደሚ የኪነ-ጥበብ አፍቃሪያን በአፅንዎት ገልፀዋል ።
ሙሉዓለም የአማራ ባህል ማዕከል
ጥቅምት 2015 ዓ.ም