ወላጆች ልጆችዎን ዕሁድን የት ለማዝናናት አስበዋል??
ሁሌም የልጆቸዎ ደስታ ደስታችን ነው ። ሙሉዓለም የአማራ ባህል ማዕከል ልጆችን በመልካም ስነ-ምግባር ታንፀው እንዲያድጉ የሚያስተምርና
ቁምነገር የሚያስጨብጥ አዲስ የህፃናት ቴአትር አዘጋጅቷል ። ከእርሰዎ የሚጠበቀው ፕሮግራመዎን ከወዲሁ ማስተካከል ብቻ!!
የጫካዋ እመቤት እያዝናና ቁም ነገር የሚያስጨብጥ የህፃናት ቴአትር በሙሉዓለም የአማራ ባህል ማዕከል
እሁድ ጥቅምት 27/2015 ዓ.ም ከጥዋቱ 4:00 ጀምሮ ከተለያዩ አዝናኝና አስቂኝ ጨዋታዎች ጋር ለዕይታ ይበቃል ።
ወላጆች ከልጆቻችሁ ጋር በመገኘት እንድትታደሙ በአክብሮት ተጋብዛችኋል ።