ሙሉዓለም የባህል ማዕከል ተተኪ የኪነ-ጥበብ ሙያተኞችን ለማፍራት ስልጠና በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

በማዕከሉ ትውፊታዊ ትውን ጥበባት ጥናት፣ምርምርና ስልጠና ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በሙዚቃም ሆነ በቴአትር ዘርፍ ተተኪ የኪነ-ጥበብ ከያኒያንን ለማፍራት የሚያስችል፣ ክፍተት የለየና አቅምን ሊያጎለብት የሚችል ተግባራዊ ስልጠና ከመስከረም 18/2014 ዓ.ም ጀምሮ እየሰጠ ይገኛል፡፡የስልጠናው የቆይታ ጊዜ ለ25 ቀናት የሚቆይ ሲሆን እስከ ጥቅምት 12/2014 ዓ.ም ድረስ እንደሚቆይ ታውቋል፡፡

ማዕከሉ ለሰልጣኞች የሚሠጣቸዉ የስልጠና ዘርፎችም፡-

  1. በተውኔት ድርሰት አፃፃፍ፣
  2. በትወና ሙያ፣
  3. በባህላዊ ውዝዋዜ፣

4.በመሰረታዊ የሚዚቃ ፅንሰ ሀሳብ እና በባህላዊ የሙዚቃ መሳሪያ አጨዋወት ስልጠና የሚሰጥ ሲሆን ከባህር ዳርና ከተለያዩ አካባቢ የመጡበአጠቃላይ 151 ሰልጣኞች በስልጠናዉ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ ፡፡

ተተኪዎችን ለማፍራት ስልጠና ወሳኝ መሳሪያ ነው!!

ሙሉዓለም የባህል ማዕከል

መስከረም 27/2014 ዓ.ም

ባህር ዳር